የእንጀራ አሰራር
ከመጸሃፉ "Taste of Ethiopia"
ከአገር ውጭ እንጀራ ለመጋገር የዳበረ ልምድ
የሚደባለቁት ተእህል አይነቶችና መጠኖች፤
- ሁለት ብርጭቆ የጤፍ ዱቄት
- ሁለት ብርጭቆ ነጭ የስንዴ ወይንም የገብስ ዱቄት
- አንድ ተኩል የስኳር ምንኪያ ቤኪይንግ ፓውደር
- አምስት ብርጭቆ ሞቅ ያለ ውሃ
- የጤፍ ዱቄቱ በሁለት ተኩል ብርጭቆ ውሃ ተቦክቶ ይቀመጣል።
- የስንዴው ወይም የገብሱ ዱቄት ግማሸ የስኳር መንኪያ
ቤኪይንግ ፓውደር ይገባበትና በብሌንደር ውስጥ ተዋህዶ
በሳህን ውስጥ ይቀመጣል።
- ሁለቱ ቡኮዎች ተከድነው ከ2 እስከ 3 ቀን እንዲያቀሩ
ይቀመጣሉ።
- ቀኑ ከደረስ በኋላ ቀስ ተብሎ የቀረረውን ውሃ ከሁለቱም
ሳህኖች ውስጥ ማፍሰስ።
- ሁለቱም እህል (ጤፍ እና ስንዴ/ገብስ) አቀላቅሎ መለውስና
እህሉ ኩፍ እስኪል ድረስ ለ2 ሰዓት ያህል ማስቀመጥ።
- ከዚያ በኋላ 425 ዲግሪስ ፍ በሞቀ መጋገሪያ አየር
እንዳይገባ ቶሎ እየከደኑ እንጀራውን መጋገር።